22/10/2025
ይህ ድርጊት መሀል አዲስ አበባ ገርጂ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርቲ መታጠፊያ መብራት ላይ አንዲት ሴት ዲዛየር መኪና እያሽከረከረች መጥታ ትቆማለች። ሁለት ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች ሴትዮዋን ከመኪናዋ ጎትተው ከአስፓልት ወርውረው ከጣሉዋት በኋላ መኪናዋን ቀምተው ለማምለጥ ይሞክራሉ። በዚህ ጊዜ ትራፈክ ፖሊሱ ያይና ሳይረን እያስጮኸ በሞተር ይከተላቸዋል። የተደናገሩት ሌቦች ለማምለጥ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲነዱ ከአንዲት ቪትዝ መኪና ጋር ይጋጫሉ። በዚህ ጊዜ ትራፊክ ፖሊሱ ይደርስና ግብግብ ይገጥማል።በአካባቢው ሰው ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተጎዳችው ባለ መኪናም ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።
እነዚህን ዘራፊዎች በማየት በመከታተል አሳዶ ታግሎ በመያዝ የጀግና ተግባር የፈፀመው ትራፊክ ሽልማት ይገባዋል ምስጋናችን ይድረሰው።
ከሾፌሮች አንደበት